ያለንን የተፈጥሮ ጸጋ በአግባቡ ከተጠቀምን ውጤታማ መሆን እንደምንችል በግል ባሀብቶ እየለማ ያለው ሰብል ማሳያ ነው ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በጉራጌ ዞን በበላይነህ ክንዴ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እየለማ ያለ የቅባት ሰብል እየጎበኙ ነው። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው እንደገለጹት ያለንን የተፈጥሮ ጸጋ በአግባቡ ከተጠቀምን ውጤታማ መሆን እንደምንችል በግል ባሀብቶ እየለማ ያለው ሰብል ማሳያ ነው ብለዋል። በክልሉ ከዚህ ቀደም ለልማት ስራ ያልዋለ እና በረሀማ በሆነ አካባቢ የኢትዮጵያን ምርት ሊያሳድግ እና ለዘይት ፋብሪካ በግብአትነት የሚችል የቅባት እህል በስፋት እየለማ መሆኑን ተናግረዋል። በሀገሪቱ ተፈላጊነቱ እየጨመረ ያለውን የዘይት ምርት ለማሳደግ የቅባት ሰብሎችን ማልማት ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ርዕሰ ጠቁመዋል። በክልሉ እየተንቀሳቀሱ ያሉ አልሚ ባለሀብቶች ለህብረተሰቡ በስራ እድል ፈጠራ፣በመሰረተ ልማት አቅርቦት እና በሌሎችም መስኮች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እያደረጉ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተደድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንደገለጹት ግብርናውን ለማዘመን እና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለማስቀረት ዘርፈ ብዙ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። ለኢንዳስትሪ ግብአት የሚሆን የሱፍ፣የሰሊጥ ፣የአኩሪ አተር እና ሌሎች ሰብሎችን በስፋት የሚያመርቱ ባለሀብቶችን መፍጠር መቻሉን አቶ ኡስማን አስረድተዋል። በክልሉ ያለውን ጸጋ ለአልሚ ባለሀብቶች ምቹ በማድረግ እና የግብርና ኢንቬስትመንት ወደ የላቀ ደረጃ በማሸጋገር ሀገራችን ለሌሎች ሀገሮች መርዳት የምትችልበትን እድል ለመፍጠር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። ባለሀብቱ በላይነህ ክንዴ በጉብኝት መርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት ከድህነት ጋር ታርቀን መኖር ይበቃናል ብለዋል። ባለሀብቱ መሬትን ጉልበትን እና ውሃን አቀናጅተን ከሰራን ያለንን የድህነት ታሪክ በአጭር ጊዜ መቀየር እንችላለን ብለዋል።በጉራጌ ዞን እየተካሄደ ባለው ኢንቬስትመንት 400 ዜጎች የስራ እድል ፈጥረናል ሲሉም ጠቁመዋል። የበላይነህ ክንዴ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 1ነጥብ 5 ሚሊየን ዘይት ያመርታል ይህም የሀገሪቱን 60 በመቶ የዘይት ምርት እንደሚሸፍን ባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ አብራርተዋል። መስክ ጉብኝቱ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሀብቶች ተገኝተዋል።