ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩል
- በክልሉ ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ ለመፍጠር የሚያስችሉ የፖሊሲና የአፈጻጸም እርምጃዎችን ያመነጫል፣ አግባብ ባለው አካል ሲጸቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣
- በክልሉ ውስጥ የሚገኘውን የሀብት ክምችትና የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች መረጃ ከሚመለከታቸው አካላት ይሰበስባል፣ ይተነትናል፣ ያሰራጫል፣ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ፕሮፋይሎችን ያዘጋጃል፣ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣
- ለኢንቨስትመንት የተለየ መሬት ተረክቦ በመሬት ባንክ ይይዛል፣ በመስተዳድር ምክር ቤቱ ሲፈቀድ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት ሕግ አግባብ ያስተላልፋል፣
- የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ሲቀርቡ አግባብ ባለው ሕግ መሰረት ገምግሞ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ይለውጣል፣ ይሰርዛል፣ የኢንቨስትመንት ስምምነቶችና ማሻሻያዎች መዝግቦ ይይዛል
- ለኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ቅልጥፍና የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ይዘረጋል፣ ያደራጃል፣ ያጠናክራል
- አግባብ ባለው የኢንቨስትመንት ሕግ መሰረት በኢንቨስትመንት ለተሰማሩ ባለሀብቶች የተፈቀዱላቸውን ማበረታቻዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
- ኢንዱስትሪዎች የድጋፍ ፓኬጅ ያዘጋጃል፣ ያቀናጃል፣ ያስፈጽማል በስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
- ኢንዱስትሪዎች ላይ ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን በጥናት ለይቶ በማቀናጀት እዲስፋፉ ያደርጋል፤ ተመሳሳይነት ያላቸውን ትስስር እንዲኖር ይሰራል፣
- ለኢንዱስትሪ ልማት የሚውሉ የክልሉ የመሬትና የተፈጥሮ ሀብት ላይ ከሚመለከተው አካል ጋር ጥናት ያካሄዳል፡ የጥናቱ ውጤት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፡ ሲጸድቅ በስራ ላይ ያውላል፣
- ኢንዱስትሪ መንደሮች፣ ሼዶች፣ ፓርኮች እና ክላስተሮች እንዲስፋፉ፣ እንዲጠናከሩ ያደርጋል፣ አስፈላጊውን ቁጥጥር ያደርጋል፣
- የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ተደራሽነት እና ምርታማነት ለማጠናከር ከሚመለከተው አካል ጋር ይሰራል፣ መካከለኛ ስልጠና ያለው የሰው ኃይል እንዲያገኙ ያመቻቻል፣
- በክልሉ ውስጥ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ስርጭት ተመጣጣኝ እና ባላቸው የልማት እድሎች ላይ የተመሠረቱ እንዲሆን ከሚመለከተው አካል ጋር ይሰራል፣ ለኢንዱስትሪው አከባቢ ማህበረሰብ ውጤታማ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣
- የማኑፋክቸሪንግ ምርቶችን ወደ ውጪ በመላክ ላይ ለተሰማሩ ፋብሪካዎች እና ኢንተርኘራይዞች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ምርታቸውን ለውጭ ሀገር እንዲያቀርቡ ያግዛል፣
- የኢንዱስትሪ የሙያ ብቃት መመዘኛ ህጎችን በስራ ላይ ያውላል፣ የጥራትን እና የምርቶችን ስታንዳርድ ከሚመለከተው አካላት ጋር በመሆን በምስክር ወረቀት ያረጋግጣል ፣ የምርት ጥራት ደረጃ እንዲያገኙ ይሰራል፣
- የኢትዮጲያዊያንና ትውልደ ኢትዮጲያውያን ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ይደግፋል፣ ያበረታታል፣ያስተባብራል፣ አፈጻጸማቸውን ይገመግማል፣ በሪፖርት ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፤
- ዓላማውን ለማስፈጸም የሚችሉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣