Skip to main content

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ  ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ ዓላማ እና ዕሴት

ተልዕኮ

የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት አገልግሎታችንን በማዘመንና በማሳለጥ የሴክተሩን  አቅም በማሳደግ አፈጻጸማቸውን በመከታተልና የሚከሰቱ ችግሮች ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመቀናጀት የሚፈቱበትን አሰራር በመቀየስ ኢንቨስትመንትንና ኢንዱስትሪዉን በማስፋፋት ዉጤታማነትን ማረጋገጥ ነዉ፡፡

ራዕይ

በ2022 ዓ/ም ለኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ልማት የላቀ ምቹ ሁኔታ የተፈጠረበት፣ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ የሆኑና ለኢኮኖሚዉ ልማት ድርሻቸዉን የሚያበረክቱ ባለሀብቶችና ኢንዱስትሪያሊስቶች እዉን ሆነዉ ማየት፡፡

ዓላማ

በክልላችን ኢንቨስትመንት በማስፋፋት፣የማምረት አቅም በማሳደግ፣ጥራት ያለውና ተፈላጊ ምርት በማስፋት፣የሥራ ዕድል በመፍጠና የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር በማፋጠን የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ  ነው፡፡

ዕሴት

  •      የሕዝብ ተጠቃሚነትን ማስቀደም፤

  •      ፍትሃዊ፣አሳታፊና አካታች ዲሞክራሳዊ አመራር፤

  •      የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት፤

  •      ሰው ተኮርነት፤

  •      ለጊዜ ከፍተኛ ዋጋ መስጠት፤

  •      ጥራት፣ፍጥነት፣ግልፅነት፣ታማኝነትና ተጠያቂነት፤

  •      ሁሌም መማርና መሻሻል፤

  •      የአካባቢ ደህንነትና ወደፊት ተመልካችነት፤

  •      በቅንጅት መስራትና ወጪ ቆጣቢነት፤

  •      አድማጭነት፣ምላሽ ሰጪነትና ተገማችነት፤

  •      ተቋማዊ ልህቀት፣ለህግና ለመርህ ተገዥነት፣የላቀ አገልግሎት፣ውጤታማነት፣ተገልጋይን ማርካት፤