በተቋሙ የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- የሀብት ክምችትና የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎችን ጥናት በማካሄድ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ የማድረግ አገልግሎት፣
- የማማከር አገልግሎት፣
- በተለያዩ የአሰራር መመሪያዎችና ማኑዋሎች ላይ ስልጠና የመስጠትና ተደራሽ የማድረግ አገልግሎት፣
- መረጃ በማሰባሰብ፣ በመተንተን እና በማደራጀት የማሰራጨት አገልግሎት፣
- የፕሮጀክት ፕሮፋይሎችን በማዘጋጀት ተደራሽ የማድረግ አገልግሎት፣
- ለኢንቨስትመንት አገልግሎት የሚውል መሬት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ማዘጋጀት፤
- የክልሉን የኢንቨስትመንት ፖቴንሺያል በጥናት የመለየትና የማስተዋወቅ ስራ ያከናውናል፡፡
- ከውጭ ሀገር መጥተው ኢንቨስት ለሚያደርጉ ዲያስፖራናየውጭ ዜጎች ድጋፍ ማድረግ፣
- ለኢንቨስትመንት የተለየ መሬት ተረክቦ በሕግ አግባብ የማስተላለፍ አገልግሎት፣
- የኢንቨስትመንት ፈቃድ የመስጠት፣የማደስ፣የመለውጥ እና የመሰረዝ አገልግሎት፣
- ኢንቨስትመንት ስምምነቶችና ማሻሻያዎች/ማስፋፊያ/ ምዝገባ የማካሄድ አገልግሎት፣
- በኢንቨስትመንት ለተሰማሩ ባለሀብቶች የተፈቀደላቸውን ማበረታቻዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ አገልግሎት፣
- ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዳስትሪዎች የድጋፍ ፓኬጅ አገልግሎት ይሰጣል፤
- የማኑፋክቸሪን ምርቶችን ወደ ውጪ ለሚልኩ ባለሀብቶች የገበያ ትስስር እንዲፈጠር የድጋፍና ክትትል አገልግሎት መስጠት፡
- የማምረቻ ኢንዳስትሪ ማዕከላትን የማስተዳደር አገልግሎት፤
- የኢንዳስትሪ የሙያ ብቃት መመዘኛ ህጎችን በሥራ ላይ እንዲውሉ የማድረግ አገልግሎት፤
- የኢንዳስትሪ ዩንቨርስቲ ትስስር እንዲፈጠር ድጋፍ የማድረግ አገልግሎት፤
- በግል ኢንዳስትሪ ፓርኮችን ለሚገነቡ ባለሀብቶች የግንባታ ዲዛይን የማቅረብ አገልግሎት፤