የኢንቨስትመንት ፈቃድ ነክ አገልግሎቶች አሰጣጥ ቅድመ ሁኔታዎች
አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለመስጠት
- የሥራውን ምንነት የሚገልጽ የፕሮጀክት ፕሮፖዛል፤
- በፕሮፖዛሉ ከተመዘገበው ጠቅላላ ካፒታል ቀሪ ሂሳቡ 30% የሞላና የቅርብ ጊዜ 6 ወራት እንቅስቃሴ የሚያሳይ የባንክ ሰቴትመንት፤
- ባንክ መረጃው በማህበር የሚቀርብ ከሆነና ማህበሩ ከተመሰረተ ስድስት ወር ካልሞላው ወይም የንግድ ስራ እንቅስቃሴ ከሌለው የፕሮጀክቱ 30 በመቶ በአካውንት መኖሩን የሚገልጽ የባንክ ደብዳቤ፣
- የባንክ ማስረጃው ከውጭ አገር የሚቀርብ ከሆነ ስለባንኩ ትክክለኛነት በዚያ አገር የውጭ ጉዳይ መ/ቤት፣ ወይም በዚያ አገር ያለው የኢትዮጵያ ኢመባሲ፣ ወይም በአገራችን የሚገኘውየዚያ አገር ኢምባሲ ማረጋገጫ የሰጡበት ማረጋገጫ፣
- ለሀብቱ በውጭ አገር ነዋሪ ሆኖ የካፒታል አቅሙን በአገር ውስጥ የሚያሳይ ከሆነ ወቅታዊ የሆነ ፓስፖርትና በባንክ 30 በመቶ ያለው ስለመሆኑ ማረጋገጫ፣ ለስራው የሚያስፈልጉ እቃዎች ወይም ማሽነሪ ተገዝቶ ከሆነ የግዢውን ሰነድ በማቅረብ የባንክ መረጃውን የሚተካ በአይነት ማቅረብ (ከ30 በመቶ የላነሰ)፣
- ወቅታዊ የሆነ የነዋሪነት መታወቂያ ካርድ እና ሦስት ጉርድ ፎቶ ግራፍ፤
- ህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፤ መተዳደሪያ ደንብ፤ የንግድና የስም የምዝገባ ሰርተፊኬት እና የግብር መክፍያ መለያ ቁጥር/ሰርተፍከት/
- በክልል ደረጃ ለሚሰጥ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከዞን/ከልዩ ወረዳ ኢንቨስትመንት መ/ቤቶች ድጋፍ ደብዳቤ፤
የማስፋፍያ ፈቃድ ለመስጠት
ሀ. የማስፋፍያ የፕሮጀክት ፕሮፖዛል እና የተጨማሪ ካፕታል የባንክ ስቴትመንት
ለ. ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ፤
ሐ. የነባር ድርጅቱ የፀና የንግድ ሥራ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ፤
መ. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ወይም ሰርተፍኬት ምስክር ወረቀት
ሠ. በቀደሞው ፕሮጀክት ያለውን አፈጻጸም የሚያሳይ የድጋፍ ደብዳቤ ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ወይም እውቅና ባለው ባለሙያ የተዘጋጀ ወቅታዊ ኦዲት ሪፖርት፡፡
ከመሬት ጋር የተያያዘ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሲወጣ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታ
ሀ. ከመንግስት በሚሰጥ መሬት ኢንቨስት የሚደረግ ከሆነ የክልሉ መንግስት በካቢኔ መሬቱ ለባለሀብቱ እንዲተላለፍ የወሰነበት ደብዳቤ፣
ለ. በግል ይዞታ ከሆነ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ እና የከተማ መሬት ከሆነ ለፕሮጀክቱ የታሰበው መሬት ለፕሮጀክቱ አግባብነት ያለው ስለመሆኑ በይዘታ ማረጋገጫው ላይ የተገለጸ፣
ሐ. በኪራይ መሬት ኢንቨስት የሚደረግ ከሆነ በሚመለከተው አካል የፀደቀና ቢያንስ የአስር አመት የኪራይ ውል፣
መሬት ለማያስፈልጋቸው የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሲወጣ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፡-
1. ለአድስ ፈቃድ የተጠየቁ መስፈርቶች እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪ፣
2. ፈቃዱ በክልል ደረጃ የሚሰጥ ከሆነ የልዩ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ፤ በባለ ኮከብ ደረጃ ሆቴል፣ ሎጅ፣ ሪስቶራንት ሞቴል እና ሪዞርት ደረጃ ፈቃድ ለመስጠት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፡
1. የሌሎች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስፈርት እንደተጠበቀ ሆኖ፤
2. ድርጅቱ በግል ይዞታ ኢንቨስት የሚደርግ ከሆነ ለፕሮጀክቱ የታሰበው መሬት ለፕሮጀክት አግባብነት ያለው ስለመሆኑ በይዞታ ማረጋገጫው ላይ የተገለፀ ሰነድ
የቡና መፈልፈያ ኢንዱሰትሪ ለማቋቋም፡ የግንባታ ካርታ ለማፀደቅና ዝውውር ለማድረግ ቅድመ ሁኔታዎች
1. የቡና መፈልፈያ ኢንዱሰትሪ ለማቋቋም
ሀ. ለአድስ ፈቃድ የተጠየቁ መስፈርቶች እንደተጠቀ ሆኖ በተጨማሪ፣
ለ. ከዞን፣ ከልዩ ወረዳ ወይም ወረዳ ግብርናና ገጠርልማት፣ ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከጤና : ከውሀና መስኖ፤ ከመሳሰሉት ድጋፍ ደብዳቤ እና የጥናት ሰነዶችን ማቅረብ፡፡
2. የእሸት ቡና መፈልፈያ የግንባታ ካርታ ለማፀደቅ፣
ሀ. የኢንቨስትመንት ሰርተፍከት፣
ለ. ፕሮጀክቱ ሲፈቀድ የተካሄዱ የጥናት ሰነዶች ከቡናና ሻይ ባለሥልጣን ማቅረብ፣
ሐ. በስታንዳርድ የተሰራ የፕላን ብሉ ፕሪንት በሁለት ኮፕ ማሰራት፡፡
3. የእሸት ቡና መፈልፈያ እንዱስትሪ ዝውውር ለማድረግ፡-
ሀ. በሽያጭ፣በውርስ፣ በስጦታ ዝውውር የተደረገበት የፀደቀ ማስረጃ፣
ለ. በቀደመው ባለሀብት/ድርጅት ስም ተሰርቶ የፀደቀው ብሉ ፕሪንት፣
ሐ. በመቋቋም ላይ የነበረ ፕሮጀክት ከሆነ በተዛወረለት ባለሀብት ስም የተለወጠ/የተሰጠ የኢንቨስትመንት ሰርተፊከት፣
መ. ማምረት/አገልግሎት መስጠት ከጀመረ የንግድ ስራ ፈቃድ በአድሱ ባለሀብት ስም የተመዘገበ፣
ሠ. የፕላኑን ብሉ ፕሪንት በሁለት ኮፒ ማሰራት፡፡
ማዕድን ነክ ውጤቶችን በግብኣትነት ወይም በጥሬ ዕቃነት በመጠቀም የማምረት አግልግሎት ለመስጠት ጥያቄ የሚያቀርቡ ባለሀብቶች፤
ለአድስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለማውጣት የተቀመጡ መስፈርቶች እንደተጠበቀ ሆኖ ከክልል ወይም ከዞን ማዕድንና ኢነርጂ መ/ቤት የሥራ ፈቃድና ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለመንግስት የልማት ድርጅትና ለህብረት ሥራ ማህበር ሲሆን፣ለመንግስት የልማት ድርጅት በሚሆንበት ጊዜ ለአድስ ፈቃድ የተጠየቁ መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆኖ፡-
ሀ. የልማት ድርጅቱ የተቋቋመበት ደንብ ፎቶ ኮፒ ወይም የመመስረቻ ጽሁፍና የመተዳደርያ ደንብ፣
ለ. የድርጅቱ ወቅታዊ ስራ አስኪያጅ ወይም ድርጅቱን ካቋቋመው አካል ማስረጃና የመታወቂያ ፎቶ ኮፒ፣መቅረብ አለበት የህብረት ሥራ ማህበርበሚሆንበት ጊዜ ለአዲስ ፈቃድ የተጠየቁ መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆኖ፡-
- የማህበሩ መተዳደርያ ወይም መመስረቻ ደንብ የጸደቀ ፎቶ ኮፒ፤
- የድጋፍ ደብዳቤ ከአደራጁ መስርያ ቤት፤ማቅረብ አለባቸው፡፡
በኢንዳስትሪ ፓርክ የሚሰጥ ፈቃድ
በኢንዳስትሪ ፓርኮች የሚሰጥ ፈቃድ በተመለከተ ለአድስ ፈቃድ የተጠየቁ መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆኖ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖረሽን የድጋፍ ደብዳቤ እና ውል የገባበት ሰነድ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለማደስ መሟላት ያለባቸው ዝርዝር ቅድመ ሁኔታዎች፡-
የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለማደስ፡-
1. ዋናው የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሠርተፊኬት፣
2. ጥያቄው የቀረበው በወኪል ከሆነ የውክልና ማስረጃ፣
3. የእድሳት ወቅቱ ያለፈበት ከሆነ ፕሮጀክቱ ምርትና አገልግሎት መስጠት ለምን እንዳልጀመረና ወደፊት ሊተገብር የሚችል ስለመሆኑ ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
ለኢንቨስትመንት ፈቃድ ለውጥ፣ ምትክና ስረዛ ጥያቄዎች መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
1. የስም ዝውውር ከግለሰብ ወደ ማህበር ለማድረግ የሚከተሉትቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው፡-
ሀ. መሬት ከሰጠው አካል የድጋፍ ደብዳቤ፣
ለ. የማህበሩ አባላት የተስማሙበትና የፀደቀ ቃለ-ጉባኤ፣
ሐ. ማሻሻያው ወይም የለውጡ መመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ የጸደቀ፣
መ. የዋና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
ሠ. ፕሮጀክቱ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ከሆነ ተቀይሮ የተሰጠበት የንግድ ፈቃድ፣
ረ. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ወይም ሰርተፍኬት፣
ሰ. የቀደመው ባለሀብት ከገቢ ግብር እና ከተለያዩ ዕዳዎች ነጻ ስለመሆኑ ከሚመለከተው አካል ማስረጃ፤
ሸ. የቀድሞው ኢንቨስትመንት ፈቃድ ምስክር ወረቀት፣
ቀ. ጥያቄው በወኪል የቀረበ ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማረጋገጫ፣
ተ. የከተማ ኢንቨስትመንት ከሆነ ፕሮጀክቱ በግንባታ ላይ ያለ ስለመሆኑና የዘመኑን የቦታ ኪራይ የከፈለ ስለመሆኑ ማረጋገጫ፣
ቸ. የገጠር ኢንቨስትመንት ከሆነ በውሉ መሰረት ወደ ልማት የገባ ስለመሆኑና የዘመኑን የመሬት ኪራይ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ማረጋገጫ መቅረብ አለበት፡፡
2. በሽያጭ ወይም በስጦታ ዝውውር ለማድረግ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፡-
ሀ. በውልና ማስረጃ የፀደቀ የሽያጭ ወይም የስጦታ ስምምነት ማስረጃ፣
ለ. ዋና የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
ሐ. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ወይም ሰርተፍኬት፣
መ. የቀድሞው ኢንቨስትመንት ሠርተፊኬት፣
ሠ. የተቀየረበት የንግድ ፈቃድ
ረ. የግዢ ወይም የስጦታ ተቀባይ የቅርብ ጊዜ ሦስት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
ሰ. የግብርና ፕሮጀክት ከሁነ የፕሮጀክቱ ልማት 50 በመቶ የሆነ ስለመሆኑ ማስረጃ፤
ሸ. በፍቃዱ ስም ብድር የወሰደ ከሆነ የአበዳሪው ክፍል አስተያየት፣
ቀ. በወኪል የቀረበ ከሆነ በውልና ማስረጃ የተሰጠ የውክልና ማረጋገጫ፡፡
3. በውርስ ምክንያት ስም ዝውውር ለማድረግ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች›፡-
ሀ. የማመልከቻ ቅጽ መሙላት፣
ለ. በፍርድ ቤት የፀደቀ የወራሽነት ማረጋገጫ፣
ሐ. ወራሾች ከአንድ በላይ ከሆኑና በአንደኛው ስም የኢንቨስትመንት ፍቃድ እንዲወጣ ከፈለጉ ሥልጣን ባለው አካል የፀደቀ የውል ስምምነት፣
መ. የወራሽ የቅርብ ጊዜ ሦስት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
ሠ. የኢንቨስትመንት ፍቃድ ወይም ሰርተፍኬት፣
ረ. ዋና የንግድ ምዝገባ ምስክ ወረቀት፤
ሰ. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ወይም ሰርተፍከት፣
ሸ. በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማረጋገጫ፡፡
4.የጠፋ ወይም የተበላሸ ሰርተፊኬት ምትክ እንደገና ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፡-
ሀ. ማመልከቻና የተበላሸውን ሰርቴፊኬት፣
ለ. በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማረጋገጫ፣
ሐ. ከፖልስ የተሰጠ ማስረጃ/ለጠፋ ሰርቴፍከት፡፡
5. ለኢንቨስትመንት ፈቃድ ስረዛ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎቸ፡-
ሀ. ለመሰረዝ ያስፈለገበትን ምክንያት ያዘለ ማመልከቻ፣
ለ. የፕሮጀክቱ አንቅስቃሴ በተመለከተ ከምገኝበት ዞን መግለጫ፤
ሐ. የኢንቨስትመንት ፍቃድ ምስክር ወረቀት፤
መ. በኢንቨስትመንት ፍቃድ የተገኙ ጥቅሞችና የተገቡ ግዴታዎችን በደንቡ መሰረት የተወጣ ስለመሆኑ ማረጋገጫ፣
6. የፕሮጀክት ለውጥ ለማድረግ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፡-
ሀ. ፕሮጀክቱ እንዲለወጥ መሬቱን ከሰጠው አካል በምን ፕሮጀክት መተካት እንዳለበት የሚገልጽ የስምምነት ደብዳቤ፣
ለ. ለውጡን ማድረግ ያስፈለገበት ምክንያት የሚገልጽ የጽሁፍ ማመልከቻ፣
ሐ. የአድሱን ፕሮጀክት ምንነት የሚገልጽ ፕሮፖዛል፣
መ. የቀድሞው የኢንቨስትመንት ሰርተፊከትና ሶስት ጉርድ ፎቶ ግራፍ፡፡
7. የካፒታል ለውጥ ለማድረግ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፡-
ሀ. የካፒታል ለዉጥ ያስፈለገበትን ምክንያት የሚገልጽ የጽሁፍ ማመልከቻ፣
ለ. በተጨማሪዉ ካፒታል የሚሰሩ ስራዎችን ምንነት የሚገልጽ አድስ ፕሮፖዛል፣
ሐ. ለተጨማሪ ካፕታል 30 በመቶ የሚያሳይ የባንክ ስቴትመንት፣
መ. የቀደመዉ የኢንቨስትመንት ሰርተፊኬትና ሦስት ጉርድ ፎቶ ግራፍ፡፡
የኢንቨስትመንት ፈቃድ የሚሰጥባቸው ተቋማት፡-
የኢንቨስትመንት ፈቃድ የሚሰጠው በኢንቨስትመንት መስሪያ ቤት ብቻ ሆኖ በክልልና በዞን ተለይተው የሚሰጡ ፈቃዶች አሉ
- ማናቸውም ከልዩ ወረዳ የሚቀርቡ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች እና በኢንዱስትሪ ፓርክ የሚስተናገዱት በክልሉ የኢንቨስትመንት እና ኢንዳስትሪ ልማትቢሮ ነው፡፡
- የእሸት ቡና መፈልፈያ ካርታ ማጽደቅ በክልል ደረጃ ብቻ የሚስተናገድ ሲሆን ሌሎች ከዞን የሚቀርቡ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ጥያቄዎች አስፈላጊውን ሂደት እና መስፈርት ባሟላ መልኩ በዞኖች ደረጃ የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡