የመዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ተቋማዊ ዳራ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ክልሉ የአስፈጻሚ ቢሮዎችን ማቁቋሚያ፣ ስልጣን እና ተግባርን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 199/2015 መሰረት የተቁቋመ መንግስታዊ ተቋም ነው። ቢሮው በክልል ደረጃ በሁለት ዘርፎች እና በስድስት የወል ዳይሬክቶሬቶች የተዋቀረ ሲሆን የወል ዳይሬክቶሬቶችም እንደ ስራው አስፈላጊነት ተደራጅተው ተግባራቸውን ሲወጡ ቆይተዋል። በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች የኢንቨስትመንትና ኢንዱስተሪ ልማት መዋቅሮች ተደራጅተው ከቢሮው ጋር በመቀናጀት ተግባራቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።ቢሮው በአዲሱ ክልል በአዋጅ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ እንዲሁም በቀድሞ የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/ ስር በነበረበት ጊዜ የኢንቨስትመንት እና የኢንዱስትሪ ልማትን በማስፋፋት የክልሉን ህብረተሰብ ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ በሰፊዉ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። እንዲሁም በከተሞች የመሰረተ ልማት በተሟሉባቸው አካባቢዎች የኢንዱስትሪ እና የአገልግሎት ሰጪ ሴክተሮች ተጠናክረው ኢንዲስፋፉ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካለትና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ስራ ለመስራት እንቅስቃሴ ተደርጓል። በተለይ በክልሉ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በተስፋፉባቸው አካባቢዎች በርካታ ዜጎች የስራ ዕድል፣ የቴክኖሎጂ እና የክህሎት ተጠቃሚ ሆነዋል። እንዲሁም ለክልሉ ወደ ስራ የተሰማሩ ባለሃብቶች መንግስት ገቢ ግብር በመክፈል እና ተኪ ምርቶችን በማምረት ለክልሉ ብሎም ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት የድርሻቸውን ሲወጡ ቆይተዋል። ባጠቃላይ ቢሮው እነዚህንና መሰል ግቦችን በማሳካት በአዋጅ የተሰጡትን ተግባራት በአግባቡ በማከናወን የተሰጠውን ሃላፊነት እየተወጣ ዛሬ ላይ ደርሷል።