የአምራች ኢንደስትሪው ማጠናከር ለሃገሪቱ የኢኮኖሚ ሽግግር ወሳኝ ነው፦የማእከላዊ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትና ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ። የአምራች ኢንደስትሪው ማጠናከር ለሃገሪቱ የኢኮኖሚ ሽግግር ወሳኝ መሆኑን የማእከላዊ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትና ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ ገለጸ። ቢሮው በማምረት አቅም ልኬት፣በደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ፣በዘርፍ ማህበራትና ምክር ቤት አደረጃጀት ዙሪያ ከዞንና ከልዩ ወረዳ ለተወጣጡ ባለድርሻ አካላት በወልቂጤ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።የማእከላዊ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትና ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር አባስ መሃመድ ስልጠናውን አስመልክተው ባደረጉት ንግግር አዲሱ የአምራች ኢንደስትሪ ፖሊሲ ክላስተርን መሰረት ያደረገ ኢንደስትሪ ማስፋፋት ነው። በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልልም አከባቢያዋ ጸጋዎችን መሰረት በማድረግ የኢንደስትሪ ክላስተር ለማስፋፋት የመሬት ዝግጅት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሎዋል። በተለይም የአምራች ኢንደስትሪው ማጠናከር ለክልሉ ብሎም ለሃገሪቱ የኢኮኖሚ ሽግግር ወሳኝ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነም ነው ዶ/ር አባስ የገለጹት። ስልጠናው ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ መሆኑም ከወጣው መረሃ ግብር ለማወቅ ተችሎዋል።