ፈቃድ የተሰጣቸው ፕሮጀክቶች ብዛት በዘርፍ ሲታይ 114 በግብርና፣ 101 በአገልግሎት እንዲሁም 76 በኢንዱስትሪ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ አባስ መሐመድ (ዶ/ር) አስረድተዋል።
በበጀት አመቱ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከተሰጣቸው ፕሮጀክቶች መካከል 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ያስመዘገቡት 48 ዲያስፖራ ባለሃብቶች መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።
የኢንቨስትመንት ፈቃድ ያወጡት 291 ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ ሲገቡ ለ43 ሺህ 283 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ማስመዝገባቸውን ጠቁመዋል።
ከዚህ ባሻገር በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ 10 ቢልየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 133 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መስፈርቱን አሟልተው ለልማት የጠየቁት መሬት ተላልፎላቸው ወደ ተግባር እንዲገቡ በክልሉ መንግሥት ውሳኔ መሰጠቱን ሃላፊው አስረድተዋል።
እንደ ቢሮ ሃላፊው ገለጻ ክልሉን የኢንዱስትሪ ሃብ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት በበጀት አመቱ ተዘግተው የነበሩ 11 ፋብሪካዎች በተደረገላቸው ድጋፍ ወደ ስራ እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም ለ41 አምራች ኢንዱስትሪዎች የ691.816 ሚሊየን ብር የስራ ማስኬጃ ብድር የተሰጠ ሲሆን ለምግብና መጠጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች ፣ማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂና ኢንጅነሪንግ እንዲሁ
ም ለኬሚካልና ኮንስትራክሽን በድምሩ 1,167,797.25 ቶን ግብአት እንዲቀርብ የማመቻቸት ስራ መከናወኑን አክለው ገልጸዋል፡፡
ዘገባው የቢሮው ኮሚኒኬሽንና ሚዲያ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው፡፡