AdminInvest
Tue, 08/05/2025 - 13:51
አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የግብ ስምምነት መፈራረማቸው ተገለጸ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ በተገኙበት የፕላን መሰረተ ልማት እና የመንግስት ሀብት አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ታመነ ገብሬ ከክልል ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር በ2018 እቅድ ላይ የግብ ስምምነት ተፈራረሙ
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ከንግድና ገበያ ልማት፣ከኢንቬስትመንት እና ኢንዱስትሪ ልማት፣ከፕላን፣ከትራንስፖርትና መንገድ ልማት፣ከፋይናንስ ፣ከገቢዎች፣፣ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን እንዲሁም ከዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የስራ ኃላፊዎች ጋር በ2018 በጀት ዓመት እቅድ የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል።