እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2017 በጀት አመት በአጠቃላይ የስራ አፈፃፀም 1ኛ በመሆኑ ከኢንዱስትሪ ሚንስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መላኩ አለበል እጅ የእውቅና ሰርተፊኬትና ሽልማት ተሰጥቶታል። በመድረኩ ተገኝተው ሽልማቱን የተቀበሉት የቢሮው ሀላፊ ዶ/ር አባስ መሐመድ እንዳሉት ይህ ውጤት ሊገኝ የቻለው የሴክተራችን የክልል ፣የዞንና የልዩ ወረዳ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የዞን፣ ከተሞችና ወረዳዎች መዋቅር አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የክላስተራችንና የክልላችን ጠቅላላ አመራሮች ባደረጉት ቅንጅታዊ ስራ ነው። በተጨማሪም የዚህ ስኬት ዋነኛ ባለቤት የሆኑት በክልላችን በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው የሚገኙ ኢንቨስተሮች እንዲሁም ህዝቡ እና ባለድርሻ አካላት ለውጤቱ መገኘት ያሳዩት የጋራ ጥረት፣ ቲም ስፕሪት፣ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት መኖር ወሳኝ እንደነበር ገልጸዋል ። በመጨረሻም ዶ/ር አባስ መሐመድ በቀጣይም አንደኛነታችንን በማስጠበቅና ፍጥነት በመጨመር ክልላችንን የኢንዱስትሪ ሀብ የማድረግ ህልማችንን ለማሳካት ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪያቸውን አስተላልፈው ለተገኘው ስኬት ሁላችንም እንኳን ደስ አለን ብለዋል። ስንተባበር ከዚህ የበለጠ ማድረግ እንችላለን! ፈጣሪ አገራችንና ህዝባችንን ይባርክ!