በክልሉ ከኢንዱስትሪው ዘርፍ በተጨማሪ በዝቅተኛ የመሬት መጠን ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ተጠቅመው በግብርናው ዘረፍ መሰማራት የሚፈልጉ ባለሃብቶችን ተቀብሎ ማስተናገድ የሚቻልበት አግባብ አለ፡፡ እንዲሁም ቀጥሎ በተዘረዘሩት የአገልግሎት የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም እና በሌሎችም ዘርፎች ባለሃብቶች ሊስተናገዱ የሚችሉበት ሰፊ እድል አለ፡፡
አገልግሎት ዘርፍ
• የኮከብ ደረጃ ያለው ሆቴል፣ሪዞርት፣ሞቴል፣ሎጅ
• የኮከብ ደረጃ ያለው ሪስቶራንት፣
• የአስጎብኝነት አገልግሎት፤
• ትምህርትና ስልጠና ከመዋእለ ህጻናት እስከ ቴክኒክና ሙያ፤
• የጤና አገልግሎት ከክልኒክ እስከ ቴርሸሪ የልዩ ሆስፒታል አገልግሎት፤


