በክልሉ በስፋት የሚገኙ የአኢንዱስትሪ ግብአቶችን ተጠቅሞ ቀጥሎ በተዘረዘሩት የኢንዱስትሪ ዘርፎች ገብቶ ኢንቨስት ማድረግ የሚቻልበት ምቹ ሁኔታ አለ፡-
• የምግብ ዘይት ማቀነባበር፣
• ስጋና የስጋ ውጤቶችን ማቀነባበር፤
• አዮዲን የተጨመረበት ጨው ማምረት፤
• ተቆልቶ የተፈጨ ቡና ወይም የሚሟሟ ቡና ማምረት፤
• የእንሰሳት መኖ ማቀነባበር፤
• የመጠጥ ኢንዳስትሪ ማቋቋም፤
• የተለያዩ የጨርቃጨርቅ ጭረቶችን ማዘጋጀት፤መፍተል፣መሸመን፣ማጠናቀቅና ማተም፤
• ቆዳና ሌጦ ማለስለስ ማጠናቀቅ እና ማተም፤
• የቆዳ ውጤቶችና ተጓዳኝ አካላትን ማምረት፤
• የቆዳ ወይም የቆዳ ምትክ ጫማ ማምረት፤
• የእንጨት ውጤቶች ኢንዳስትሪ ማቋቋም፤
• የማተሚያ ኢንዳስትሪ መቋቋም
• የኬሚካልና የኬሚካል ውጤቶች ኢንዳስትሪ ማቋቋም፤
• የመሰረታዊ መድኃኒት ምርት እና የመድኃኒት ፋብሪካ ማቋቋም፤
• ብረት ያልሆኑ የማእድን ውጤቶች ኢንዳስትሪ ማቋቋም ለአብነት መስታወተወ/የሴራሚክ ውጤቶች፡፡
• የመሰረታዊ ብረታ ብረት ኢንዳስትሪ ማቋቋም፤
• ለስትራክቸር የሚያገለግሉ የብረታ ብረት ውጤቶች ኢንዳስትሪ ማቋቋም፤
• የኮምፒውተር፤የኤሌክትሮኒክስ እና የእይታ እቃዎች ኢንዳስትሪ ማቋቋም፤
• የማምረቻ/አገልግሎት መስጫ መሳሪያዎችና ዕቃዎች ኢንዳስትሪ ማቋቋም፤
• የቤትና የቢሮ እቃዎች ማምረት
• የእደ ጥበብ፣የገጸበረከት እቃዎች፤አርቴፊሻል ጌጣጌጥ የሙዚቃና የስፖርት እቃዎች ማምረት