በክልሉ የሚገኙ የኢንዳስትሪ ጥሬ እቃ/ግብአት አቅርቦቶች
ክልሉ ለተለያዩ የአግሮ ፕሮሰሲንግ አገልግሎት የሚውሉ የግብርና ውጤቶች የማምረት ከፍተኛ አቅም አለው፡፡ ለአብነትም በክልሉ በዋነኛነት ከሚመረቱ የብርዕና አገደ ሰብሎች በቆሎ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ጤፍ ከጥራጥሬዎች አተር፣ ባቄላ፣ ሽምብራ፣ ከተለያዩ ፍራፍሬዎች ሙዝ፣ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ አፕል፣ አናናስ፣ ከስራ ስር ሰብሎች እንሰት፣ድንች፣ ጎደሬን ከቅባት እህሎች ደግሞ ኑግ፣ሱፍ፣ሰሊጥና ቦሎቄን ከአትክልት ቲማቲምና ሽንኩርትን መጥቀስ ሲቻል ለቡና፤ ለዝንጅብል፣ ለሮዝሜሪ እና ለተለያዩ ቅመማ-ቅመሞች ወዘተ ተስማሚ የአፈርና አየር ንብረት የሚገኝበት ክልል ሲሆን እንደ ጠንባሮ ልዩ ወረዳና አንዳንድ የክልሉ አከባቢዎች ደግሞ ቅቤና ማር በሰፊ ይመረታል፡፡ ለኢንዱስትሪ ክፍለ ኢኮኖሚ ሊውሉ የሚችሉ እንደ ክሌይ፣ የድንጋይ ከሰል፣ የብረት ማዕድን፣ ካኦላይን፣ ላይም፣ የጌጣ ጌጥና የግንባታ ማዕድናት በክልሉ ይገኛሉ፡፡ አሸዋ፣ ጥርብ ድንጋይ፤ የኖራ ድንጋይ እና የመሳሰሉት የኮንስትራክሽን ግብአቶች በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች በስፋት ይገኛሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የክልሉ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ የኢንዳስትሪ ጥሬ እቃ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የግብርና ውጤቶች እና የተፈጥሮ ማዕድኖች በከፍተኛ ደረጃ ከሚገኝባቸው ክልሎች ከኦሮሚያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያና ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ጋር የሚዋሰን በመሆኑና ለአዲስ አበባባና ለሞጆ ደረቅ ወደብ ካለው ቅርበት አንጻር ከሌሎች አከባቢዎች በተሻለ ሁኔታ የኢንዳስትሪ ጥሬ እቃዎች ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር ገበያ ለማስገባት ልዩ እምቅ አቅም ያለው መሆኑ ክልሉን ፍጹም ተወዳዳሪ ያደርገዋል፡፡
በምግብ ማቀነባበር ኢንቨስትመንት ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀበቶች ክልሉ ያለው ልዩ አቅም
ከፍተኛ የስንዴ አምራች በሆኑት ሙሉሀዲያ፤ ስልጤ ከፊል ጉራጌ፤ሀላባና ከምባታ ዞኖች እንዲሁም በማረቆ ቀቤና እና ጠምባሮ ልዩ ወረዳዎች ለፓስታ ማካሮኒ በስኩትና መሰል ምግቦችን ለማቀነባበበር በቂየኢንዳስትሪ ጥሬ እቃ አቅርቦት ያለባቸው አከባቢዎች ናቸው፡፡ በወተትና የወተት ውጤቶች ማቀነባበር ለሚሰማሩ ባለሀብቶች በወተት ተፋሰስነት በሚታወቁትና በተመረጡት እንደ ከምባታና ሀዲያ በመሳሰሉት ዞኖች ቢሰማሩ ለሚቋቋመው ኢንዳስትሪ የተሻለ ግብአት የሚገኝባቸው አከባቢዎች ሲሆኑ የአትክልትና ፍራፍሬ ውጤቶችን በማቀነባበር ለሚሰማሩ የግል ባለሀብቶች የጉራጌ፤ የምስራቅ ጉራጌ፣ የከምባታ ዞኖችና የጠምባሮ ልዩወረዳ በአንጻራዊነት የተሸለ እድል ያላቸው አከባቢዎች ናቸው፡፡ የዶሮና የእንሰሳት ስጋን በመቀነባበር በማሻግ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች የጉራጌ፤የስልጤ፣ የከምባታና የሀዲያ የም ዞኖችና የቀቤና ልዩ ወረዳ በአንጻራዊነት የተሻለ የኢንዳስትሪ ጥሬ እቃ ግብአት ለማቅረብ ምቹ አከባቢዎች ከመሆናቸውም በላይ በተቀሩትም የክልሉ አከባቢዎች ምቹእድሎች አሉ፡፡


